ደቀ መዝሙር 102/Discipleship 102

ማቴቴስ - ደቀ መዝሙር ምን ማለት ነው?

“ደቀ መዝሙር” ማለት ተማሪ ወይም ተከታይ ማለት ነው። ደቀ መዝሙር የሚማረው ለማወቅ ብቻ ሳይሆን ያወቀውን በተግባር ለማዋል ነው። በየዘመኑይኖሩ የነበሩ ታላላቅ አስተማሪዎች ደቀ መዛሙርት ነበሩዋቸው። ለምሳሌ፦ ኢያሱ የሙሴ ደቀ መዝሙር ነበረ። የግሪኰች ፈላስፋ ፕሌቶ የሶክራጥስ፤አሪስቶትል ደግሞ የፕሌቶ ደቀ መዛሙርት እንደ ነበሩ ከታሪክ እንረዳለን።

 • ደቀ መዛሙርት ማፍራት የጌታ የኢየሱስ ትዕዛዝ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
 • ደቀ መዛሙርት ለማፍራት የጌታ ደቀ መዛሙርት ልንሆን ያስፈልጋል።
 • ደቀ መዛሙርት ለማፍራት ወደ አሕዛብ ሁሉ መሄድ ያስፈልጋል።
 • ደቀ መዛሙርት ለማፍራት ያመኑትን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ማጥመቅ ያስፈልጋል።
 • ደቀ መዛሙርት ለማፍራት ጌታ ያዘዘውን ሁሉ እንዲጠብቁ ያመኑትን ማስተማር ያስፈልጋል።
ደቀ መዛሙርት ለማፍራት ስንሰማራ ጌታ ሁልጊዜ በመጀመሪያ ምዕተ ዓመት መጀመሪያ ደግሞ መጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርት እንደ ነበሩትና ከደቀመዛሙርቱ አንዳንዶቹ የጌታ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆኑ ከአዲስ ኪዳን ጽሑፎች እንገነዘባለን። (ዮሐንስ 1፡35-40)
ኢየሱስ ዓለም አቀፍ የሆነውን የማዳን ዓላማውን ለማዳረስ ሕዝቡን ከማስተማር ሌላ አስራ አንድ ደቀ መዛሙርት አሠልጥኗል። አስራ አንዱ ደቀ መዛሙርትበመንፈስ ቅዱስ መሪነትና ረድኤት የወንጌል መልእክት ዛሬ የደረሰበት ሁኔታ ላይ አድረሰዋል።
ወንጌልን ወደ ዓለም ሁሉ የማድረስ ተግባር ዛሬም ገና አላበቃም፤ ወንጌል ያልሰሙ፣ ሰምተውም ያልገባቸው፣ ገብቷቸው ተገቢ ምላሽ ያልሰጡ ገና ብዙሰዎች አሉ። ወንጌልን ወደ ዓለም ሁሉ ለማድረስ ዋነኛ መንገድ በመንፈስ ቅዱስ መሪነትና ረድኤት ደቀ መዛሙርት ማፍራት ነው።
 1. የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ፣ ደቀ መዝሙርነት በመጀመሪያ ለጌታ መታዘዝን ቀጥሎም እርስ በርስ መታዘዝን ይጠይቃል፣ ይላል። ራሳችን ለጌታ ሳንታዘዝሌሎች እንዲታዘዙን እየጠበቅን ይሆን?
 2. ደቀ መዝሙርነት ዋጋ የሚያስከፍል ሕይወት ነው። ዋጋውን ተምነን እናውቃለን? ለመክፈል ፈቃደኞች ነን?
 3. ድብቅ አኗኗርና የጐደለ የሕይወት ምስክርነት ደቀ መዝሙር ለመሆን ሆነ ደቀ መዛሙርት ለማፍራት አያስችለንም። ለሚያዩን ፈለግ የሚሆን ሕይወትአልተገኘብን ይሆን?
 4. እነ ጴጥሮስ የመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት ነበሩ። ራሳችንን ከነርሱ ተራ ለመመደብ ምን መብት አለን?
 5. የሰው ቁጥር በየቤተ ክርስቲያኑ መብዛት ስለ ደቀ መዝሙርነት ምን ያስረዳናል? የዮሐንስ ወንጌል 6፡66 ይመልከቱ።
 6. ሌሎች ጌታን ታዝዘው የምሥራቹን ወንጌል እንዳመጡልን ማስታወስ ለምን ይጠቅማል?
 7. እውነተኞች ደቀ መዛሙርት ለመሆን አኗኗራችንን እንዴት ልናስተካክል ይገባል?
 8. ሰባኪና አስተማሪን ምን ይለያቸዋል?
 9. ባለንበት ቤ/ክ የማስተማር ጸጋ የተሰጣቸው አሉ? ይህንስ ጸጋ አክብረው ይጠቀማሉ?
 10. በማስተማር የሚያገለግሉ ጥቂት መሆናቸው ማስተማር የሚጠይቀውን ትዕግስትና ኃላፊነት ለመቀበል ካለመፍቀድ የተነሳ ይሆን? አኗኗራችን የሩጫበመሆኑ ይሆን? የማንበብና የማጥናት ልምድ ከማጣት ይሆን? ከምንገኝበት ሁኔታ ጋር ለማገናዘብ ካለመቻል የተነሳ ይሆን?


Your Instructor


Asfaw Bekele (Rev.)
Asfaw Bekele (Rev.)

Frequently Asked Questions


When does the course start and finish?
The course starts now and never ends! It is a completely self-paced online course - you decide when you start and when you finish.
How long do I have access to the course?
How does lifetime access sound? After enrolling, you have unlimited access to this course for as long as you like - across any and all devices you own.
What if I am unhappy with the course?
We would never want you to be unhappy! If you are unsatisfied with your purchase, contact us in the first 30 days and we will give you a full refund.

Get started now!